ጎጎት ለጉራጌ አንድነት እና ፍትሕ ፓርቲ የፓርቲውን የፊት አመራሮች ባደረገው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው መርጦ ይፋ አደረገ።

መጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በተካሄደው ምስረታ ጉባዔ በጠቅላላ ጉባኤተኞች የተመረጡትን ሃያ ዘጠኝ (29) ቋሚ እና ሰባት (7) ተለዋጭ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት ይፋ ተደርጓል።

በጠቅላላው ጉባኤተኛ በተሰጠው ድምፅ ከፍተኛውን ድምፅ ያገኙ 29 ተወዳዳሪዎች የፖርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሆነው ዛሬ ጠዋት በይፋ ስራ ጀምረዋል።

በዚህም መሰረት የስራ አስፈፃሚ ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር መርጧል። ፓርቲውን በሊቀመንበርነት አቶ መሃመድ አብራር በምክትል ሊቀመንበርነት ደግሞ በአሁን ሰዓት በቡታጀራ ከተማ በእስር እሚገኙት አቶ እንዳለ ንዳ እንዲመሩት ተመርጠዋል።

በአስራ አንድ (11) አባላት የተዋቀረው የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ የፓርቲውን ፅህፈት ቤት እንዲመሩ በዋና ፅህፈት ቤት ኃላፊነት አቶ እንዳልካቸው አወል እና በምክትል ፅህፈት ቤት ኃላፊነት አቶ መላኩ ሳህሌ መርጦ አስፈላጊውን ሰነዶች በቦታው ለተገኙ የምርጫ ቦርድ ታዛቢ በማስረከብ የእለቱ ስብሰባ ተጠናቋል።