የጉራጌ ማህበረሰብ ከትውልድ ትውልድ የተላለፉ ልዩ ልዩ አባባሎችን ያካተተ የበለፀገ ባህል ባለቤት ነው። ቃዋ ፕሬስ እነዚህን የጉራጌ አባባሎች ስብስብ አሳትሞ ለህዝብ ተደራሽ ለማድረግ ፍላጎት አለው። ስለ ጉራጌ አባባሎች እውቀትም ሆነ መረጃ ካላችሁ በቃዋ ፕሬስ በኩል እንድናትመው ሼር በማድረግ እንድታካፍሉን እንጋብዛለን። ዛሬ ለቃዋ ፕሬስ  አስተዋፅዖ ካበረከቱት አንዷ ሳምራዊት ክብሩ ያበረከቱትን ጥቂት የጉራጌ አባባሎች ስናካፍለ ደስ እያለን ነው።

1. ጉራጊኛ= በአብ አፈር ይትዋኴ በአዶት አፈር ይትሻኮቺ

አማርኛ =በአባት መሬት ይዋጋሉ በእናት መሬት ይታረቃሉ

2.  ጉራጊኛ =አብ ኤባር ንበረት ወካ ኤነን ቤት እማቱ

 አማርኛ = አባት የሌለበት ኑሮና መሶሶ የሌለው ቤት አንድ ነው

3. ጉራጊኛ = አት ኧጨ ኤረድድ እማት ምስ ኤፈርድ

 አማርኛ = አንድ እንጨት አይነድም አንድ ሰውም አይፈርድም

4. ጉራጊኛ = አትᎊጠᎀዊም ቢሞኲ ተጌከረም ነማም

አማርኛ = አስጎንብሰው በቀብሩት ተስተካክሎ በቀለ

5. ጉራጊኛ = አናከረ ቃውጣ አንቃታ በኤብ ያጣጣ

አማርኛ = ከብት ያላረባ ጉረኛ አፉን በወተት ይለቃለቃል

6. ጉራጊኛ = አንቅም ወለብነት ኤትሼምታ

 አማርኛ =ሃቅና ጨዋነት አይሸሸግም

7. ጉራጊኛ = አቦገዳ ቲኸዳ የቸኮሪ በሰር አንበራ ይብር

 አማርኛ = ጓደኛ ሲከዳ የተቀቀለ ስጋ አልበላም ይላል

8. ጉራጊኛ = ያጀጎረን ታጀጎረን ይትጮድ

አማርኛ = የቸገረው ከተቸገረ ጋር ይወያያል

9. ጉራጊኛ = አንፊና ቲደርጒ ኤን ይበሂ

 አማርኛ = አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል