ዘቢዳር ቲዩብ እንደዘገበዉ

ሚያዚያ 7 2016

በተደራቢ መዝገብ ተከሰው የፌደራል ወልቂጤ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ቀርበው የነበሩት አቶ ታረቀኝ ደግፌ እና አቶ ሃይደር ሙራድ በጠየቁት የዋስትና መብት ጉዳይ ውሳኔ ለማስተላለፍ የዛሬ ሳምንት ሚያዝያ 14/2016 ቡታጀራ ከተማ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ተቀጥረዋል።

ተከሣሾች የተከሰሱበት መዝገብ ከዚህ ቀደም ቡታጀራ ከተማ ላይ ታስረው የነበሩ ተጠርጣሪዎች የተከሰሱበት እና የዋስትና መብት የተከበረበት መሆኑን በመጥቀስ ዝርዝር ሃሳባቸውን በፅሑፍ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ ቀጣይ ቀጠሮ ለአንድ ወር ግንቦት 12 ሰጥቶ የነበረ ሲሆን ተከሳሾች እስካሁን ለተራዘመ ፍትሕ ሰለባ መሆናቸዉንና በጊዜ ቀጠሮ በማረሚያ እየታሹ መሆኑን ገልፀው በመሞገታቸው ፍርድ ቤቱ የግራና ቀኝ ዳኞች መክረው የዋስትና ብይን ለመስጠት ወደ ቀጣይ ሳምንት ቀጠሮዉን አሳጥሮታል። አቃቤ ህግም የተከሳሾችን ፅሁፍ መቃወም ከፈለገ ሚያዝያ 12 በፅሁፍ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በተመሠሣይ የፍርድ ቤት ዜና ወልቂጤ ከተማ ላይ ተፈፅሞ ከነበረው ጥቃት ጋር በተገናኘ ክስ የተመሰረተባቸው 86 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱም ክስ ተመስርቶባቸው ያልቀረቡ ተከሳሾች ፖሊስ አሟልቶ እንዲያቀርብ አዞ መዝገቡን ለነገ ጠዋት ቀጥራል። በዚህ መዝገብ 11 ተከሳሾች የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ 75 ተከሳሾች የቀቤና ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች መሆናቸው ይታወቃል።

ይህ ፁፍ ዘቢዳር ቲዩብ ላይ የቀረበ ነዉ።