
ፊታ አውራሪ ሳፎ በጉራጌ ዞን በጘታ ወረዳ ቀቡል ቀበሌ ልዩ ስሙ አጀሟዘር በሚባል ቦታ 1889 ዓ.ም ተወለዱ። አባታቸው አዝማች ጄጀነ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ ምድርወት ይባላሉ፡፡
እኚ አባት በጉራጌ ብሎም በደቡብ አካባቢ ለሚኖር ህዝብ መብት መከበር ታግለዋል።
የመንግስት ሹም በመሆን በሰባት ቤት ጉራጌ በሁሉም ወረዳዎች ላይ በምክትል አስተዳደርነት ሰርተዋል። በተለይም በወለኔም በምክትልነት ሲሰሩ ጊዜ ሽፍታ ከአካባቢው በማፅዳት ይታወቃሉ።
በአርበኝነት ዘመን በማይጨው ጦርነት ግንባር ቀደም በመሆን ለሀገራቸው ተዋድቀዋል።
የጣሊያን ጦር ኢትዮጵያን ሊወራት በመጣ ጊዜ በጉራጌና በስልጤ ያለውን ሀይል በመምራት ወረራውን አክሽፈዋል እንዲሁም በሙጎ ተራራ ላይ በፋት ለፋት ጦርነት ድል ነስተውታል፡፡ከከምባታ እስከ ጅማ በነበረው የጠላት ጦር ላይ ጉዳት አደወርሰዋል።
ፊት አውራሪ ሳፎ ማዕረጉ የተሰጣቸው በቤተ-ጉራጌ ያለው የድንበር ሁኔታን በማስተካከልና ጉራጌን በሚያስተዳድሩበት ጊዜ ዋቤን ከጠላት እጅ የመለሰ ጀግና በሚል የፊት አውራሪነት ስም ተሰጥተዋቸዋል፡፡
ቀሪ ዘመናቸዉን አበጃ በሚባለው መንደር ትዳር መስርተው ኖረዋል። በዚህ አካባቢም በርካታ አዳዲስ ስራዎችን ሰርተዋል። በዚህም አቀጥየ መድሃኒያለም ቤ/ክ አሳንፀዋል።
በኃላም የቋንጤ ት/ት ቤት መስርተዋል ለጉራጌ ህዝብ አስረክበዋል። በሀገር ሽማግሌነታቸውም አንቱታን ያተረፋ ታላቅ አባት ነበሩ።
ፊት አውራሪ ሳፎ በተወለዱ በ96 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
የዚ ፁፍ ምንጭ የጌታ ወረዳ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ።
