መቼም ለሚወዱት ነገር የሚከፈለው ዋጋ እንዲሁ በቀላሉ የሚተመን አይደለም። ደሳለኝ መርሻም የገጠመው ይህ ነው።

የመጀመርያ አልበሙ ያሳተመው አዲስ አበባ ውስጥ የታክሲ እረዳት እየሰራ ባለበት ወቅትነበር። ያኔ አንድ ሙዚቃ አልበም ለማሳተም የሚያስፈልገው ወጪ ይህ ነው አይባልም።

ይህ ሁሉ ውጣውረድ 7ተኛውን የጉራጊኛ አልበም ማለትም ኑድኒያን አስመርቃለሁ ብሎም አስቦም አያውቅም . . . የደሳለኝ መርሻ

ህይወት ጥሪውን ተከትሎም ከዚህ ቀደም ስድስት አልበሞችን ማለትም “ፍረህ ደነና በ1994 ዓ.ም፤ “መገናኘ 19961 ግነኖ 19981 “አያርሴ” 2001፣ “ሒታኒያ 20041 “ያሚያሚና 2009 ዓ.ም ለሙዚቃ ቤተሰቡ አድርሷል። ባለፉት 20 አመታትም ሙዚቃን ሕይወቱ በማድረግ ለበርካታ ድምፃውያንም ግጥም እና ዜማዎችን ሰጥቷል::

ያ ሁሉ ልፋቱ ከነ ጋሽ መሀሙድ አህመድ፣ ከ ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ እና ከሌሎች አንጋፋ ድምፃውያን ተርታ እንዳሰለፈውም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በሙዚቃዎቹ የጉራጌ እሴቶችን፣ ታሪክ፣ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ሕይወትን በተባ ኪናዊ ለዛ በመሰነድ እና በማስተዋወቅ የራሱን አሻራ አኑሯል፡፡ ጉራግኛ መስማት የማይችሉ ሰዎች አንዱ የሚያጎድሉት ነገር ቢኖር በደሳለኝ የሙዚቃ ግጥሞቹ ውስጥ ያሉ የፖለቲካ፣ የባህል፤ ማህበራዊ ጉዳዮች ውስጥ ያሉ አስገራሙ ፍልስፍናዎችና እይታዎች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
በአሁኑ ሰአት አርቲስት ደሳለኝ መርሻ ቁጥር 7 የሙዚቃ አልበሙን ይለቃል፡፡ እጅግ ፈታኝ የሙዚቃ አለም ውስጥ እያለፈ ያለው ይህ አዲሱ አልበም፣ ደሳለኝ መርሻ ራሱ ከሰራቸው የቀደሙት ስድስት ሆኑ ሌሎች አቻ ስራዎች በተለየ መልኩ አዳዲስ የሙዚቃ ቴክኒኮችና የጉራግኛ ሙዚቃ ጠቅላላ መልክ የሚቀይር ስራችን በመስራት ላይ በመሆኑ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ይሆናል፡፡
አልበሙ 13 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስለፍቅር፣ ስለሃገር፣ ስለማህበራዊ ህይወት የሚዳስስ ሁለገብ አልበም ነው፡፡ እልበሙ ላይ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ በግጥም እና ዜማ እራሱ ደሳለ” መርሻ፣ ፈለቀ ማሩ፣ ናቲ ኃይሌ፤ ዘነበ መርሃባ፤ ሀብታሙ አብርሃም፥ አለማየሁ ወልዴ የተሳተፉ ሲሆን በቅርንብር አሌክስ ይለፍ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፤ ሰማገኘው ሳሙኤል፤ ፋኑ ጊዳቦ፤ ቢኒእነዴ ርሆቦት (ሮባ) የተሳተፉ ሲሆን በሚክሲንግ ሰለሞ™ ሃ/ማርያም፣ ፍሬዘር ታዬ፣ መሀመድ ኑርሁሴን፣ ቢኒአንዴ ተሳትፈዋል፡፡ ማስተሪንግ ሰለሞን ሃ/ማርያም የአሸነው ሲሆ በአርቲስቱ Desalegn Mersha ዩ-ቲዩብ ቻናልና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያ ይገኛል፡፡ ሲዲውን ኪነ ኢንተርቴይመንት አሳትሞ ያከፋፍለዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ኑድኒያ ማለት የተወደደች እንቁ ሴት ማለት እንደሆነ ሰምተናል።

የዚ የዜና ምንጭ ሰበር ዜና ነዉ። ይህ ፁፍ ከFacebook ገፃቸዉ የተወሰደ ነዉ።