
ሰኔ 08/2016 አ. ም (ወልቂጤ ኤፍ ኤም ሬድዮ)
አርቲስት መሀመድ አወል ከ1970ዎቹ ጀምሮ ከ10 በላይ አልበሞች የሰራ፣ የጉራጌ እና ስልጤ ባህል ዘመናዊ ሙዚቃ ያስተዋወቀ፣ አዳዲስ የጉራጊኛ የሙዚቃ ስልቶችን የፈጠረ፣ በራስ ቲያትርና በሌሎች የኪነ ጥበብ ማዕከላት ውስጥ ለአያሌ አመታት በብቃት ያገለገለ ሲሆን የላቀ የሙዚቃ ሰውነቱ በሀገር ውስጥና በባህር ማዶ መድረኮች በብቃት አስመስክሯል።
“ሲጎ ሲጎሌ” የተሰኘው የመጀመርያው ነጠላ ዜማ በጉራጊኛ የሰራ አንጋፋ ከያኒም ነው። በወቅቱም ጉራጌን በአለም መድረክ ያስተዋወቀ አርቲስት ነው።
በአሁኑ ወቅት ከሙዚቃው አለም ቢገለልም በሰራቸው ስራዎች የምንግዜም የጉራጊኛ ሙዚቃ ምልክት ሲሆን በሙዚቃዎቹ ውስጥ ባነሳቸው ሀሳቦች ደግሞ የጉራጌና የአጎራባች አካባቢዎች የባህል፣ የማህበራዊ ህይወት እና የኪነ ጥበብ አባት ነው።
በመሆኑም አርቲስት መሀመድ በጉራጌ ዞን አስተዳደር፣ በጉራጌ ባህልና ልማት ማህበር እንዲሁም በጌቶ ወረዳና በሌሎች አጋር ድርጅቶች በተዘጋጀው የአረፋ በአል ልዩ ዝግጅት ላይ የምስጋናና የመሬት ስጦታ ተደርጎለታል።
በቀጣይም በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ባለሀብቶችና የበአሉ ታዳምያን ለአርቱስቱ የአገልግሎት ዘመን የሚመጥን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ቃል ተገብቶለታል።
ኢድ ሙባረክ!
በሄኖክ ተክሌ
የዚ የዜና ምንጭ ወልቂጤ ኤፍ ኤም ነዉ
